Welcome to Misrak WDDBA Level5
Now, you are in control!

ምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በከተማችን ከሚገኙ ስድስት የመንግስት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች መካከል አንዱ ነው፡፡ ኮሌጃችን በገበያ ፍላጎት መሰረት ክህሎት ያለው፣ በዲሲፕሊን የታነጸ፣ ተነሳሽነት የተላበሰና ከአዳዲስ አሰራሮች ጋር ተዋህዶ ስራውን የሚያከናውን የሰለጠነ የሰዉ ኋይል ማፍራትን ዓላማ አድርጎ ደረጃውን በጠበቀ እና በተሟላ የማሰልጠኛ ወርክ ሾፕ ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በቀን እና በማታ በቅዳሜና እሁድ መርሃግብር በሚከተሉት የሙያ ዘርፎች ከደረጃ 1- 5 ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ስለሆነም የስራና ክህሎት ሚ/ር ያወጣውን የመግቢያ መስፈርት የምታሟሉ በአካል ወይም በኦንላይን/online
Mptc.aatvetb.edu.et እንድትመዘገቡ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡
Congratulation
ምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ በ22 የሙያ አይነቶች ከደረጃ 2 እስከ ደረጃ አምስት ያሰለጠናቸውን 700 ሰልጣኞች በዛሬው እለት በሚሊኒየም አዳራሽ በድምቀት አስመርቋል፡፡ በምርቃት ስነስርዓቱም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሰለጠነ የሰው ሃይል በተለይም በክህሎት የታነጸ የስራ ባህልን መመሪያው ያደረገ የዳበረ ትጉህ ሀገሩን የሚወድ ተለውጦ የሚለውጥ የሰው ሀይል ያስፈልጋታል በዚህም የከተማ አስተዳደሩ ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ሰልጣኞች 30 ንድፈ ሀሳብ 70 የተግባር ስልጠና በመውሰድ ስልጠናቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልጸው ተመራቂ ሰልጣኞች የጨበጡትን እውቀት በራሳቸው ጥረት እያሳደጉ በመሄድ በስራ ገበያ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚገባቸውበምክትል ከንቲባ ማእረግ የሥራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ገልጸዋል፡፡



Links of interest: